“እኛ በሠላም እንድንኖር በየበረሃውና ጦር ሜዳው የተሰው ሰማዕታትን ልናስብ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ሚካኤል

223

ደብረ ታቦር፡ ታህሣሥ 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ2014 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በደብረታቦር ከተማ ተከብሯል፡፡ በበዓሉም የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብክት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡

የልደት በዓል የመገለጥና ምስጋና ቀን ነው ያሉት ብጹዕነታቸው “እኛ በሠላም እንድንኖር በየበረሃውና ጦር ሜዳው የተሰው ሰማዕታትን ልናስብ ይገባል”ብለዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምህረት ሞላ “የልደት በዓል ለሰው ልጅ እርቅና የሐጢያት ሥርየት የተደረገበት፣ ሰማይና ምድር የታረቁበት፣ የሰው ልጆችና ቅዱሳን መላዕክት በአንድ ላይ የዘመሩበት፣ ልዩ ታሪክ፣ ምስጢርና በረከት የተገኘበት ነው” ብለዋል፡፡

በበዓሉ ታድመው ያገኘናቸው ወጣት መሠረት ገበየሁና ወጣት ጊዜርቅ በሪሁን በዓሉን ስናከብር በበጎ አድራጎት ሥራዎች፣ አቅመ ደካሞችን በማሰብ እና በማገዝ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት

ዘጋቢ፡- ዋሴ ባየ – ከደብረታቦር

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ጀግና ሕዝብ – በቀኝ እጁ ድልን የሚጨብጥ፣ በግራ እጁ ይቅርታና ምህረትን የሚቸር ነው!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleከካናዳ ወደ ሀገራቸው የገቡት ዳያስፖራ ለልደት በዓል ጓደኞቻቸውን በማስተባበር ለወገን ጦር አባላት ማዕድ አጋሩ፡፡