
ላልይበላ፡ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በድል ማግስት በቅዱስ ላልይበላ ከምዕመናን ጋር የልደት በዓልን እያከበሩ መሆናቸው ታላቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ገለፁ።
አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን ተደምስሶ ከአካባቢው ከወጣ በኋላ የልደት በዓል በላልይበላ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። አሚኮ ያነጋገረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል ገዛኽኝ ባልቻ የልደት በዓልን ከወራሪው ቡድን ነፃ በሆነችው ላልይበላ ማክበር ከፍተኛ ደስታ ይፈጥራል ብሏል። በዓሉንም የአካባቢውን ሠላም እያስጠበቁ ማክበራቸውን ገልጿል። የሀገር ሰላም በዘላቂነት አስኪረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት በድል እና በጀግንነት እንደሚወጡ ነው ያረጋገጠው፡፡
የልደት በዓልን በላልይበላ ከተማ ስታከብር ያገኘናት መቶ አለቃ ትዕግስት ሰለሞን “ምእመኑ በዓልን ያለ ምንም ምድራዊ ከልካይ እንዲህ በነፃነት እና በሰላም ሲያከብር ማየት ታላቅ ደስታን ይፈጥራል” ብላለች፡፡ ይህ ሰላም እና የሕዝብ ደኅንነት ዘላቂ እንዲሆን የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ነው ያለችው፡፡
ሌላኛው አስተያየት ሠጪ ኮሎኔል ካሳሁን አሊ እንደገለፁት ሠራዊቱ በግዳጅ ወቅት እልህ አሰጨራሽ ሥራ ሠርቷል፤ በፈጸመው ጀብድም ሕዝቡ ከሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነፃ በመሆን በዓልን በነፃነት እያከበረ ነው፤ ይህ ነፃነት እንዲመጣ ልዩ ኃይሉ፣ፋኖው እና ሕዝባዊ ሠራዊቱም ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር በመሆን አኩሪ ገድል መፈጸሙን ተናግረዋል። ሁሉም በተገኘው ድል መዘናጋት ሳይገባ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ኮሎኔል ካሳሁን ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሀገር ለማፍረስ የማይተኛ በመሆኑ ሁሉም ለቀጣይ ግዳጅ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/