
ላልይበላ፡ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን እና የደቡብ ወሎ ዞኖች እንዲሁም የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ የልደት በዓልን አስመልክቶ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክ አስተላልፈዋል፡፡
ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ‹‹የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓልና የባለሟሉን የቅዱስ ላልይበላን በዓለ ልደት በቃል ኪዳን ቦታው ለማክበር የተገኛችሁ ሁሉ ለበዓሉ እንድንገናኝ እንኳን ፈቀደልን›› ብለዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ወገኖቻችን ለአምስት ወራት እህል ብቻ ሳይሆን የወገኑ ፊት ርቦት፣ ውኃ ብቻ ሳይሆን የወገን ድምጽ ጠምቶት መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
‹‹ዛሬ በዚህ ቦታ ስትገኙ ጦርነቱን ተከትሎ በመጡ ፈተናዎችና መከራዎች ተፈትኖ የነበረውን ወገናችሁን እያጽናናችሁ መሆኑን እንረዳለን፤ ለዚህም በቅዱስ ላልይበላ ደብር እና በዞናችን ማኅበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ›› ነው ያሉት፡፡
አቡነ ኤርሚያስ ሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በተወረረበት ጊዜ የወልድያ ከተማ እና አካባቢውን ሕዝብ ሲንከባከቡ የነበሩ የሕዝብ እውነተኛ አባት ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/