በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ የልደት በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

128

ላልይበላ፡ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢየሱስ ክርስቶስና የቅዱስ ላል ይበላ የልደት በዓል ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ፣ ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ
የልደትን በዓል መሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ በላል ይበላ መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የልደት በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል። በዚህ ዓመት የልደት በዓል በላል ይበላ በልዩ ሁኔታ እንዲከበር ጥሪ ተለላልፎ እንደነበርም አስታውሰዋል።

በተደረገው ጥሪ መሠረት በታላቅ ድምቀት መከበሩንም አስታውቀዋል። አካባቢው በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተወርሮ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት መከበሩንም ገልፀዋል።

በዓሉ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች በዓሉ በፀጥታ ኃይሎች ጥመረት፣ በወጣቶች እና በሰላም ወዳዱ ሕዝብ የጋራ ትብብር በሰላም መጠናቀቁን ነው የተናገሩት። የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ግዛቸው ልክ እንደ ላል ይበላ ሁሉ ጥመቅትን በጎንደር ብዙ ሕዝብ በተገኘበት በታላቅ ድምቀት እናከብራለንም ብለዋል። ክልሉ ሰላማዊ መሆኑ ታውቆ ቀጣይ በሚኖሩት በዓላት ሕዝቡ በስፋት እንዲታደምም ጥሪ አቅርበዋል።

የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች ፣ የክልሉ ሕዝብና የፀጥታ ተቋማት የልደት በዓል በላል ይበላ በሰላም እንዲከበር እንዳደረጉ ሁሉ ቀጣይ የሚከበሩ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የተለመደውን ኃላፊነት እንድትወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ልደትን በላልይበላ እንዲህ በደመቀ መልኩ እንድናከብር ውድ ሕይዎታቸውን ለከፈሉ ሁሉ ምሥጋናችን ይድረስ” የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ
Next article‹‹…በቅዱስ ላልይበላ ደብር እና በዞናችን ማኅበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ›› ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ