የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በቅዱስ ላልይበላ በቤዛ ኩሉ ሥነ-ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልእክት ያነሱአቸው ሀሳቦች

150

• ያ ሁሉ የጭለማ ጊዜ አልፎ ልደትን በላል ይበላ በዚህ መልክ እንድናከብር የረዳን ፈጣሪ ይመስገን፤
• ላል ይበላ የእምነት እና የተቀደሰ ቦታ ብቻ አይደለም፤ ላልይበላ እፁብ ድንቅ የሆነ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የባሕል እና የእምነት መገለጫ ቦታ ነው፡፡ የላልይበላ ቅርስ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው የሥልጣኔ እና የኪነ ሕንጻ ፀጋ ነው፡፡

• ላልይበላ የሰው ልጆች ምን ይሠሩ እንደነበር ጥበባቸው፣ የምህንድስና አቅማቸው፣ የት ደረጃ ደርሶ እንደነበረ የሚያሳይ፤ የቀጣዩን የሰው ልጅ ሕይወት ፈጠራ እና እውቀት የሚያነሳሳ፣ ብርሃን የሚፈነጥቅ ታላቅ እና ውድ ቅርስ ነው፡፡
• ላልይበላ የእውቀት እና የቴክኖሎጂ አሻራ ብቻ ሳይሆን የፅናትም፣ የሥነምግባርም ተምሳሌት እና መገለጫ ነው፤ ይህ የሥልጣኔ፣ የጥበብ እና የፅናት መገለጫ የሰው ልጆች ሁሉ ሃብት ነው፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደመ አንድ ትምህርት ቤት መልሶ እንደሚገነባ የአራዳ ክፍለ ከተማ አስታወቀ፡፡
Next article‹‹የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የታላቅነታችን ማሳያ ነው›› አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ