
በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ በቤተ ማርያም በኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሃይማኖታዊ ሥርዓት የሚከወነው ቤዛ ኩሉ በሊቃውንት እየተፈጸመ ነው።
በቤተ ማርያም ከማሜ ጋራ ጫፍ ላይ እና ከሥር በሥርዓት የተደረደሩ ካባና ሸማ ለባሽ ሊቃውንት የዓለም ቤዛ ተወለደ እያሉ ጌታቸውን እያመሰገኑት ነው። ከጋራው አናት ላይ የሚሆኑት በመላእክት ሲመሰሉ፣ ከምድር ያሉት ደግሞ በሰዎች (በኖሎት ) ይመሰላሉ።
ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በበረት ሲወለድ ሰውና መላእክት በጋራ ሆነው አመስግነውታል። እሰይ የዓለም ቤዛ ተወለደ ብለውታል።
ቤዛ ኩሉ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ከሚከበሩት ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች አንደኛው ነው። ቤዛ ኩሉ ከሃይማኖታዊ ሥርዓቱ በተጨማሪ የጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ ይታወቃል።
በታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/