
ላልይበላ: ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ)ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ለማክበር ላልይበላ ገብተዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በላልይበላ በብሔራዊ ደረጃ እንደሚከበር የቱሪዝም ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላልይበላ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ነው። በዓሉ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውነተ ቤተክርስቲያን እና ምዕመናን በተገኙበት ከዋዜማው ጀምሮ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ነው ሲከበር ያደረው።
እንደ ሀገር በላልይበላ የሚከበረው የልደት በዓል የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንደሚያነቃቃውም ይጠበቃል።
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴም በብሔራዊ ደረጃ የሚከበረውን የልደት በዓል ለማክበር ነው ላልይበላ የተገኙት።
በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላልይበላ እየተከበረ በሚገኘው የልደት በዓል ፕሬዚዳንቷን ጨምሮ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች ፣ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ምዕምናን ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ – ከላልይበላ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation