
ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝበ ክርሰቲያኑ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ሲያከብር የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና ጉዳት የደረሰባቸውን ሐዘናቸውን በመካፈል ሊሆን እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ።
ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ሰላም በአንድነት ሊቆሙ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
የሃይማኖት አባቶቹ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምዕምኑ በዓሉን ሲያከብር የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብ እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በዓሉን ስናከበር የተራበውን በማብላት፣ የተጠማውን በማጠጣት፣ የታረዘውን በማልበስ እንዲሁም የታመመውንና የታሰረውን በመጠየቅ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል፥ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ስናከብር በጦርነቱ የተፈናቀሉትንና ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በማሰብና ሐዘናቸውን በመካፈል ሊሆን ይገባል ብለዋል።
እያንዳንዱ ሰው ወንድምና እህቱን እንደራሱ አድርጎ እንዲወድ ታዟል ያሉት ካርዲናል ብርሃነየሱስ፤ የሰላምን ሰንሰለት ከሚበጥሱት ከትዕቢት፣ ከጥላቻ፣ ከኩራትና ከቁጣ መንፈስ መራቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በበኩላቸው፥ የልደት በዓልን ንብረታቸው ወድሞና ተዘርፎ ቤተሰቦቻቸውን አጥተው በሐዘን ላሉ ወገኖቻችን ፍቅርና አብሮነትን በሚያሳይ መልኩ ማክበር ይገባል ብለዋል።
ስለ ሰላም ማስተማርና መልካም ምሳሌ ኾኖ መገኘት ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ በመሆኑ ምዕመናን ራሳቸው ታርቀው የማስታረቅ አገልግሎታቸውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በኢትዮጵያ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ተቀራርበን መሥራት ይገባናል ያሉት ቄስ ደረጀ፥ በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መቆም እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/