
ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ለልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አቶ ግርማ ያስተላለፉት መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል፡-
ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች፣ በኅልውና ትግሉ ምክንያት በግንባር ለምትገኙ የሀገር ባለውለታ ለሆናችሁ ጀግኖች የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
የዘንድሮውን የልደት በዓል ከወትሮው ልዩ የሚያደርገው ለሦስት አስርት ዓመታት በሀገራችን እንደ መዥገር ተጣብቆ ኢትዮጵያን ሲረግጥ የነበረው ትህነግ የክልላችንን በርካታ አካባቢወች እጅግ ኋላቀር በሆነ የሕዝባዊ ማእበል የጦርነት ስልት በመውረር በወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ መጠነ ሰፊ ዘረፋና ውድመት በመፈፀም ጉዳት ሲያደርስ ከቆየበት ጊዜያቶች በመላው ኢትዮጵያዊያን ተጋድሎና በሕዝባችን ያልተቋረጠ ደጀንነት በወረራ ይዟቸው ከነበሩት የክልላችን በርካታ አካባቢዎች በሽንፈት ተገድዶ በወጣበት ማግስት ላይ የምናከብረው በዓል በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
የምዕራቡ ዓለም አንዳንድ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ይዘውት የተነሱትን አፍራሽ ተልዕኮ በ’በቃ (#Nomore)’ ንቅናቄ የሞገቱ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑ አያሌ ዳያስፖራዎች ወደእናት ሀገራቸው በመጡበት ወቅት የሚከበር በዓል መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
እብሪተኛው ወራሪ እና ዘራፊው የትግራዩ ወንበዴ ራሱ በለኮሰው እሳት የተለበለበበትና ከኢትዮጵያዊያን ትክሻ ላይ ተራግፎ የወደቀበት ወቅት ላይ እንገኝ እንጂ፣ ይህ የጥፋት መንጋ እስትንፋሱ እስካልተቆረጠ ድረስ ሕዝባችንና ሀገራችን ኢትዮጵያ እረፍት አያገኙም። ስለሆነም በሁሉም ግንባሮች የምናደርገው ተጋድሎ እና ዝግጅት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ላፍታም ቢሆን እንደማንዘናጋ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።
የምንገኝበት ወቅት የቱንም ያህል ፈታኝና ውስብስብ ቢሆንም ቅሉ ከታሪካችን እንደምንረዳው የትኛውም ጠላትና ፈተና ቢገጥመንም ከሕዝባችን ጋር ኹነን በድል አድራጊነት እንደምንሻገረው ሙሉ እምነት አለኝ።
የዘንድሮውን የልደት በዓል ስናከብርም እርስ በርስ በመደጋገፍ፣ በመተሳሰብ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን በማጠናከር በኅልውና ዘመቻው የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን በዘላቂነት በማቋቋም፣ የምንግዜም ጀግኖቻችን ለኾኑት የሰማዕታት ቤተሰቦች በመደገፍ ሊሆን ይገባል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጽልመትን የመግፈፍ፣ የተስፋና ብርሃን ምልክት እንደሆነው ኹሉ፤ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የግንባር ተጋድሎ ለኅልውናችን መረጋገጥ ብሎም ለነገ የጋራ ብልጽግናችን ዋስትና ነው።
ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች!
በድጋሜ መልካም የልደት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ!
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/