ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጡ።

181

ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ጋር መክረዋል።

በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሰለሞን ነጋሽ፣ በአትላንታ የኢንፎርሜሽን ሲስተም አርክቴክቸር ባለሙያ አህመድ ጀማል እና በ ቨርጂኒያ የመረጃ እና የመሰረተ ልማት ደኅነነት አማካሪ ፍስሃ ደስታ ሀገራቸውን በዘርፉ ለማገልገል እንደሚፈጉ ተናግረዋል።

የዲጂታል አገልግሎቶች ጥራት እና ደረጃን በማስጠበቅ፣ በዲጂታል ደኅንነት፣ በዲጂታል ኦዲትና በዲጂታል ኢኖቬሽን ላይ ያላችውን እውቀት ለማካፍል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዘርፉ የተሰማሩና በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን በማስተባበር ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ዲያስፖራዎቹ ሀገራቸውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በመምጣታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ሚኒስትር ዲኤታዋ ስለ ኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ገለፃ አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየሠራች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በዘርፉ የባለሙያዎችን አቅም ለመጠቀምና በትብብር ለመሥራት ተቋሙ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል።

ባለሙያዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሚደረገው የዲጂታል ፎረም ላይ እንደሚሳተፉ እና ተሞክሯቸውን እንደሚያጋሩ ማስታወቃቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ︎‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ ሀገር ለማፍረስ የሄዱበትን ርቀት እና እኔ እያለሁ ሀገሬ አትፈርሰም በሚል ሞትን እስከጥጉ የደፈሩ ጀግኖችን ታሪክ በአግባቡ መሰነድ ይገባል” የታሪክ እና የባሕል ምሁሩ ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያ
Next articleየልደት እና ጥምቀት በዓላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከበሩ በቂ ዝጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡