“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ ሀገር ለማፍረስ የሄዱበትን ርቀት እና እኔ እያለሁ ሀገሬ አትፈርሰም በሚል ሞትን እስከጥጉ የደፈሩ ጀግኖችን ታሪክ በአግባቡ መሰነድ ይገባል” የታሪክ እና የባሕል ምሁሩ ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያ

84

አዲስ አበባ፡ ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ታሪክ ሦስት ዓይና ነዉ፤ የትናንትን ያስታዉሳል፤ የዛሬን ያሳያል፤ የነገን ይተነብያል ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡ የዛሬ ኹነት በአግባቡ ተሰንዶ ካልተቀመጠ በስተቀር የነገዉ ትዉልድ መነሻዉንም ኾነ መድረሻዉን ለማወቅ ይቸግረዋል፡፡ ከትናንት ዉድቀቶች እና ስኬቶችም መማር የሚቻለው በተመዘገበ ኹነት ነው።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ ሀገር ለማፍረስ የሄዱበትን ርቀት እና እኔ እያለሁ ሀገሬ አትፈርሰም በሚል ሞትን እስከጥጉ የደፈሩ ጀግኖችን ታሪክ በአግባቡ መሰነድ እንደሚገባ የታሪክ እና የባሕል ምሁሩ ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር አሕመድ ኢትዮጵያ የረጅም እድሜ ባለጸጋ እና የባለ ብዙ ታሪክ ባለቤት ብትሆንም ኀላፊነት በማይሰማቸው፣ ታሪክን በሚያዛንፉ እና ስም አጥፊ በሆኑ ባዕዳን አኩሪ እና አስተማሪ ታሪኮቿ ተዳፍነዉ ቆይተዋል ብለዋል።

አሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ እንዲሁም በአማራ እና አፋር ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ክህደት እና ግፍ እንደሌላዉ ጊዜ ታሪክ ተደባብሶ እንዳይቀር ሁኔታው በማን፣ ለምን እና እንዴት እንደተፈጸመ በአግባቡ እና በጥንቃቄ ተሰንዶ ለነገዉ ትዉልድ መማሪያነት ሊቀመጥ ይገባል ይላሉ ፕሮፌሰሩ፡፡

የአሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ቡድን የእኩይ ተግባሩ ተጋሪዎች እና የአስተሳሰቡ ተሸካሚዎች ሀገርን ለማፍረስ በተሰማሩበት ወቅት እኔ እያለሁ ሀገሬ አትፈርሰም ብለዉ ሞትን እስከጥጉ የደፈሩ ጀግኖች ተፈጥረዋል፤ ሀገራቸውንም ከመፍረስ እንዳዳኑ ተናግረዋል፡፡

የከሀዲዎችን አሳፋሪ ተግባር እና የጀግኖችን አኩሪ ጀብድ ሰንዶ አለማስቀመጥ ሀገር ለማፍረስ ከተሰማሩት አሸባሪ ቡድኖች ተርታ እንደመሰለፍ ነዉም ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያ እንደነገሩን የዘርፉ አጥኝዎች በሳይንሳዊ የታሪክ ትርጉም ሕይዎት የሁለት ነገሮች ዉጤት ነች ብለው ያምናሉ፡፡ የትዝታ እና የተስፋ፤ ትዝታ ከሌለን ተስፋ ሊኖረን አይችልም፤ የትናንት ትዝታ መጥፎም ሆነ በጎ በአግባቡ መመዝገብ አለበት፤ ታሪክ መማማሪያ መዝገብ ነዉና ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡-በለጠ ታረቀኝ-ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሸባሪው ቡድን ያወደማቸውን ተቋማት መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ ባላቸው አቅም ኹሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን የዳያስፖራ አባላት ገለጹ፡፡
Next articleትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጡ።