አሸባሪው ቡድን ያወደማቸውን ተቋማት መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ ባላቸው አቅም ኹሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን የዳያስፖራ አባላት ገለጹ፡፡

101

ደሴ፡ ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል፡፡ በሽብር ቡድኑ የደረሱ ጉዳቶችን የዳያስፖራ አባላት በደሴና አካባቢው ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የሀገር ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የዳያስፖራ አባላት እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሽብር ቡድኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈፀመው ድርጊት እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

ከኦስትሪያ ቬና ወደ ሀገር ቤት የገቡት አቶ ታሪኩ ተገኘ የሽብር ቡድኑ በሀገር እና በወገን ላይ ያደረሰውን ጉዳት በርቀት ሆነው እየሰሙ ሲያዝኑ መቆየታቸውን ነግረውናል።
አሁን ደግሞ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት በአካል ተገኝተው መመልከታቸውን ገልጸው የፈጸመውን እኩይ ተግባር በቃላት ለመግለጽ እቸገራለሁ ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በተለይ ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጥላቻ እና የጭካኔ ጥግ በተግባር ያሳየበት እንደሆነም ነው የተናገሩት።

ከአሜሪካ ቺካጎ የመጡት ወይዘሮ ሳባ ሽብሩ በበኩላቸው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለጹት። ወራሪው ቡድን ዳግመኛ ጉዳትና ውድመት እንዳያደርስ ኹሉም በአንድነት መቆም አለበት ነው ያሉት።

የዳያስፖራ አባላቱ በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመቀናጀት ያላቸውን አቅም ተጠቅመው በሽብር ቡድኑ የወደሙ ተቋማትን በመልሶ ግንባታ ሥራ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በቀጣይ ኢትዮጵያዊያን በሀገር ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ረገድ ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡

ከውስጥ እና ከውጭ በሀገር ላይ የተደቀነውን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ ቆርጠው መነሳታቸውንም የዳያስፖራ አባላቱ አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፡-ተስፋሁን ታምር-ከደሴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ለመጡ የዲያስፖራ አባላት ለማስተዋወቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
Next article“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ ሀገር ለማፍረስ የሄዱበትን ርቀት እና እኔ እያለሁ ሀገሬ አትፈርሰም በሚል ሞትን እስከጥጉ የደፈሩ ጀግኖችን ታሪክ በአግባቡ መሰነድ ይገባል” የታሪክ እና የባሕል ምሁሩ ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያ