
ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በድል ማግስት ለሚከበረው የልደት በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ገለጸ፡፡
በዓሉን ተከትሎ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ የኢትዮጵያዊያን ዕሴቶች የሆኑትን ፍቅርንና አንድነታችን በማጠናከር መከበር እንደሚገባው ምክር ቤቱ አመልክቷል፤ ኢትዮጵያዊ ጨዋ ባህላችንን የሚሸረሽር መለያየትና ጥላቻን በመቅበር፣ ለጋራ ዓላማ በመትጋት፣ የተቸገሩትን በመታደግ በዓሉ ሊከበር እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞና ትንሣኤ በሚያፋጥኑ ጉዳዮች ላይ በሚደረገው ርብርብ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቤት የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጎላ ድርሻ ያለው በመሆኑ፣ ምክር ቤቱ የተጣሉበትን ሀገራዊ ኃላፊነቶች እንዲወጣ ሁሉም በተሠማራበት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
በኢትዮጵያ ኅልውና ላይ የተቃጣውን ሀገር የማፍረስ ሴራ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት መክተን ኢትዮጵያ አሸናፊ ኾና ቀጥላለችም ብሏል ምክር ቤቱ ።
በዓሉ ለኢትዮጵያዊያን ድርብ ደስታ የፈጠረ ሲሆን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዓሉን ከእኛ ጋር ለማክበር በመምጣታቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች አንገታቸውን ደፍተዋል ብሏል።
በዓሉ ለኢትዮጵያዊያን የብልጽግና፣ የደስታ፣ የሰላምና የአንድነት እንዲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መልካም ምኞቱን ገልጿል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/