በጦርነቱ ወቅት ችግር ውስጥ ለወደቁ ዜጎች ድጋፍ እንደሚደረገው ኹሉ በበዓሉ ወቅትም ያለው ለሌለው በመርዳት የልደት በዓልን እንዲያከብር ብፁዕ አቡነ በርናባስ ጥሪ አቀረቡ፡፡

117

ሰቆጣ፡ ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግኽምራ እና የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርናባስ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

“የጌታችን መወለድ የዓለም መወለድ ነው፤ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ፈጥሮናል፤ ባጠፋነው ጥፋት እና በሠራነው ስህተት ከመንግሥተ ሰማያት ከተሰደድን በኋላ እሱ በቃሉ ወደዚህ ዓለም በመምጣት ተወልዶ፣ ተጠምቆ፣ ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ተነስቶ እንደሚያድነን በሰጠው ቃል መሠረት በዲያብሎስ እጅ የነበርነውን ወደ ሕይወት የመለሰበት በዓል በመኾኑ ከሌሎቹ በዓላት በተለየ መንገድ ይከበራል” ብለዋል ብፁዕ አቡነ በርናባስ።

ብፁዕነታቸው እንዳሉት እግዚአብሔር ወደዚህ ዓለም በመምጣት በሰላም እና በፍቅር እንድንኖር መከራን ተቀብሎ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጥቷል። በዚህም ያልተረጋጋውን ዓለም አረጋግቷል፤ ያልጸናውን ዓለም አጽንቷል፤ ሰላም ያልሰፈነበትን ዓለም ሰላምን አስፍኗል፤ በዚህም ከክርስቶስ በተገኘው ሰላም የ2014 ዓ.ም የልደት በዓልን በደማቅ ኹኔታ ይከበራል ነው ያሉት።

ዓለም አሁንም በገዛ እጁ መድኃኒዓለም የሰጠውን ሰላም እና ፍቅር በራሱ ሥራ እያጣ እንደገና የመከራ ግድግዳን እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

አሁንም ከራስ ወዳድነት፣ ከጥላቻ እና ከመገዳደል ወጥተን ሰላም እና ፍቅርን ልንሰብክ ይገባል ነው ያሉት። መሪዎችም ችግሮችን በምክክር እና በውይይት ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።

በየትኛውም አካባቢ ያለው ወገንም ስለሰላም እና ስለፍቅር በመስበክ ችግሮችን ማስቆም እንዳለበት ተናግረዋል። በጦርነቱ ወቅት ችግር ውስጥ ለወደቁ ዜጎች ድጋፍ እንደሚደረገው ኹሉ በበዓሉ ወቅትም ያለው ለሌለው በመርዳት በዓሉን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ -ከሰቆጣ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
Next article❝እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)