
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት በተለይ በዓሉን በላልይበላ ስናከብር በእምነት ብቻ ሳይኾን ባሕልና ማንነትን ጨምሮ የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በላልይበላ ስናከብር ውድ የኾነውን እሴታችንን ለዓለም የምናስተዋውቅበት ነው ብለዋል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ንጹሐንን ጨፍጭፎና ብዙ ንብረት አውድሞና ዘርፎ ቢሄድም በዓሉን ስናከብር የተጎዱ ዜጎች ልብን የሚጠግን ሀብትና ንብረትን የሚመልስ ተግባር በመፈጸም አጋጣሚውን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ርእሰ መሥተዳድሩ አስገንዝበዋል።
በዓሉን በላልይበላ የሚያከብሩ በተለይ ዳያስፖራዎች ይኽን መልዕክት በመተግበር ሀብትና ንብረት የወደመባቸው ዜጎች መልሶ በሚተካበት መንገድ ላይ የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በተለየ መልኩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውንም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል።
የአማራ ክልልም ኾነ መላ ኢትዮጵያውያን በዓሉን ሲያከብሩ ከተረፋቸው ሳይኾን ካላቸው በመቀነስ የተጎዱ ወገኖች ተመልሰው እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉም ዶክተር ይልቃል ጠይቀዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/