
ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ከአሁን ቀደም የሰዓት እላፊ ገደብ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 መንቀሳቀስ እንደማይቻል ውሳኔ በማሳለፍ በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ እንደገለጹት ከአሁን ቀደም ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳደሮች በመስጠት የፀጥታ ሁኔታውን እየገመገሙ በራሳቸው ሰዓት እላፊ ገደቡን የማንሳትም ኾነ የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር የተሰጣቸው መሆኑን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
አሁን ያለውን ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የሰዓት እላፊ ገደቡን በተመለከተ አስተዳደር ምክር ቤቱ ዛሬ ውይይት አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉን ነው የገለጹት፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/