“ትምህርት ሚኒስቴር 50 ዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ያስገነባል” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

649

ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ትምህርት ሚኒስቴር በመላ ኢትዮጵያ 50 ዘመናዊ ደረጃቸውን የጠበቁ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት የሚያስችል ፕሮጀክት ማዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ።
በትምህርት ቤቶቹ የዲዛይን ዝግጅቱ ላይም ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኀበር ጋር ውይይት እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ 48 ሺህ ትምህርት ቤቶች ቢኖሩም ደረጃቸውን የጠበቁት 0 ነጥብ 01 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአጠቃላይም ስድስት ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው ደረጃ አራት ላይ የሚገኙት ብለዋል።
ስለዚህም ኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ የአካልና የአዕምሮ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤቶች ያስፈልጓታል፤ ለዚህም ደረጃቸውን የጠበቁ አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን መገንባት አለብን ብለዋል።
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኀበር በበጎ ፈቃደኝነት የትምህርት ቤቶቹን የግንባታ ዲዛይን ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ በዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክት ለመሳተፍ ፈቃደኝነታቸውን ላሳዩ ኢንጂነሮችም ምስጋና አቅርበዋል።
የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ዝግጅት በተመለከተ የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኀበር አመራርና አባላት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዜና መጽሔት ባሕር ዳር ፡ ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
Next article❝የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳደሮች በመስጠት የፀጥታ ሁኔታውን እየገመገሙ በራሳቸው ሰዓት እላፊ ገደቡን የማንሳትም ኾነ የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር ተሰጥቷል❞ የአማራ ክልል መንግሥት