ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የፌደራል ተቋማት የ100 ቀናት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በህዳሴው ግድብ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

443

ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የካቢኔ የፌደራል ተቋማት የ100 ቀናት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ላለፉት ሳምንታት የተቋማቱን አፈጻጸም በተለያየ የቁጥጥር ሥርዓቶች ሲከታተል የቆየው የፕላንና ልማት ሚኒስቴርም የእያንዳንዱን ሚኒስቴር ተቋማት አፈጻጸምን በመድረኩ አቅርቧል፡፡
ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር) እንዳሉት ሀገሪቱ ባስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብታልፍም ባለፉት 100 ቀናት በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል።
ባለፉት 100 ቀናት በግብርናው ዘርፍ የመኸር ምርት መሰብሰብ እና የመስኖ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
ከወጪ ንግድም በ100 ቀናት ውስጥ ከ800 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ባቀረቡት ሪፓርት ገልጸዋል።
ኢኮኖሚው በማክሮ ደረጃ ጥሩ ውጤት እንደተመዘገበት ቢገመገምም ሀገሪቱ ተገዳ በገባችበት ጦርነት ምክንያት ከፊቱ በርካታ ፈተናዎች እንደተደቀኑበት ሚኒስትሯ በግምገማ መድረኩ ላይ መግለጻቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ለኢትዮጵያ የምንችለውን ኹሉ የማድረግ ግዴታ አለብን❞ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ
Next article❝ሰማያዊት እና ምድራዊት ኢየሩሳሌምን በዓለት ላይ አነፃቸው❞