❝ለኢትዮጵያ የምንችለውን ኹሉ የማድረግ ግዴታ አለብን❞ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ

252

ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ያቀረቡትን የታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ በመቀበል ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብታለች።
ጋዜጠኛዋ ❝ለኢትዮጵያ የምንችለውን ኹሉ የማድረግ ግዴታ አለብን❞ ነው ያለችው።
ጋዜጠኛ ሔርሜላ አዲስ አበባ የገባችው ከወላጅ እናቷ ጋር ነው። ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰሜን፣ ደቡባዊ አሜሪካና የካሪቢያን ሀገራት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ (ዶ.ር)ን አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላታል።


ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫና በመቃወም የምትታወቀው ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ የተደረገላት አቀባበል እንዳስደሰታት ተናግራለች።
የኢትዮጵያ ምድር ከረገጥኩኝ ጀምሮ የተሰማኝ ስሜት ታላቅ ኩራት ነው ማለቷን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው በምትፈልጋቸዉ ወቅት በመገኘታቸው ምሥጋና ይገባችኋል” የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የፌደራል ተቋማት የ100 ቀናት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በህዳሴው ግድብ በመካሄድ ላይ ነው፡፡