“ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው በምትፈልጋቸዉ ወቅት በመገኘታቸው ምሥጋና ይገባችኋል” የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት

144

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት በመምጣት ለሀገር ግንባታ እያደረጉት ያለዉ አስተዋጽኦ የሚያስመሰግን መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።
ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን
ሁሉም በሙያቸው ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው በምትፈልጋቸዉ ወቅት በመገኘታቸው ምሥጋና ይገባችኋል” ብለዋል፡፡
ዶክተር ለገሰ በመግለጫቸው በኅብረ ብሔራዊ ዘመቻ የመንግሥት ጦር ባለበት እንዲጸና መደረጉን አስታውሰው የትግራይ ሕዝብ አሁንም የሽብር ቡድኑን ተግባር በጥብቅ ሊያወግዝ እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡
በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለሕዝቡ ሰላም ሊሠሩ ይገባልም ሲሉ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አንስተዋል።
በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ተፈጽሞባቸው በነበሩ አካባቢዎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ወደ ሥራ እየተመለሱ መሆኑን ዶክተር ለገሰ ቱሉ ጠቅሰዋል።
ወደ ላልይበላ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የአውሮፕላን በረራዎች መጀመራቸዉን አንስተዋል።
ዶክተር ለገሰ አሁንም ኢትዮጵያዉያን እርስ በርስ የመረዳዳት ባህልን በማዳበር በወረራ ጉዳት ለደረሰባቸዉ አካባቢዎች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
በኦነግ ሸኔ እና በድርቅ የተጎዱ የኦሮሚያ አካባቢዎችም ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።
በተጨማሪም ከሽብር ቡድኖች ጋር ቁልፍ ግኙነት አላቸዉ ተብለው የተጠረጠሩ እና በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡-ኤልሳ ጉኡሽ-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝አካባቢያችንን በተጠንቀቅ እየጠበቅን እንገኛለን❞ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የወገን ጦር አባላት
Next article❝ለኢትዮጵያ የምንችለውን ኹሉ የማድረግ ግዴታ አለብን❞ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ