❝አካባቢያችንን በተጠንቀቅ እየጠበቅን እንገኛለን❞ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የወገን ጦር አባላት

405

ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወገን ጦር ነፍጥ አያያዙንም አጠቃቀሙንም ያውቅበታል፤ ጠላት ገና ስሙን ሲሰማ ነው የሚብረከረክ፡፡ የወገን ጦር ሀገር በጠላት ስትደፈር ካዝናውን አጉርሶ፣ አፈሙዙን ወልውሎ፣ በዱር በገደል እየተዋደቀ በነበልባል ክንዱ ጠላትን እያሽመደመደ ስለ ሀገሩ የሚዋደቅ ከሀገሬ በፊት እኔን ብሎ ደረቱን ለጥይት የሚሰጥ የሀገር ዋልታ ነው።
አሸባሪው ቡድን በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ዳግም ወረራ ለመፈፀም በርካታ ጊዜ ሙከራ ቢያደርግም የወገን ጦር አባላት በነበልባል ክንዳቸው እያደቀቁ እየደመሰሱት ይገኛሉ።
በወልቃይት ጠገዴ የወገን ጦር አባል የሆነው ወንዱ ሰጠኝ ከ30 ዓመታት በኋላ የተገኘውን የነፃነት አየር አስጠብቆ ለመዝለቅ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን የኢትዮጵያ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ እንደሚቀብሩት ገልጿል፡፡
“የያዝነው የጦር መሳሪያ ስለ ሀገር ልንዋደቅበት፣ አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን ሀገር አንድነቷን ልናስጠብቅበት ነው” ብሏል፡፡ ከወገን ጦር ጋር ተቀናጅተው አካባቢያቸውን በተጠንቀቅ እየጠበቁ መሆናቸውንም ነግሮናል።

ሌላው የወገን ጦር አባሉ ሃብቱ ተሻለ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተደምስሶ ኢትዮጵያ ሰላም የምታገኝበት ቀን ሩቅ አይደለም ብሏል፡፡
ለወገን ጦር አስተማማኝ ደጀን የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋም ረገድ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አባላቱ ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ያየህ ፈንቴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የኀልውናችን ስጋት በመሆኑ ሁልጊዜም በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን መጠበቅ አለብን❞ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next article“ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው በምትፈልጋቸዉ ወቅት በመገኘታቸው ምሥጋና ይገባችኋል” የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት