
ታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የኀልውናችን ስጋት በመሆኑ ሁልጊዜም በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን መጠበቅ አለብን ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ።
ርእሰ መሥተዳድሩ ያስተላለፉት መልዕክት
ቀጥሎ ቀርቧል:-
ኅልውናችን ለማስከበር መላ ሕዝባችን ያለምንም ልዩነት በአንድነት የከፈለው መስዋእትነት የጠላትን ወረራ መቀልበስ እንዳስቻለ ኹሉ በቀጣይም ለኅልውናችን ስጋት የሆነውን ወራሪ ቡድን ለመዋጋት ብቻ ሳይሆን ለውስጣችን ሰላምና ልማትም ወሳኝ በመሆኑ አንድነታችን አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል።
በሌላ በኩል የከተሞቻችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መጀመሪያ በኮሮና ቫይረስ በመቀጠል በጦርነቱ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከሙ ይገኛሉ። ይህን የቁልቁለት ጉዞ ለመግታት የተገኙ አማራጮችን ኹሉ በመጠቀም ኢኮኖሚውን ማነቃቃት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው። ከዚህ አንጻር በመጭው ጊዜያት በተለይ የቱሪስት ከተማዎች የበለጠ እንዲነቃቁ የሚከበሩ በዓላትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የመሻሻል ተስፋን መፈንጠቅ አለብን።
ከመደበኛ አከባበሩ በተጨማሪ ዳያስፖራው ከሀገር ፍቅር ስሜት በመነጨ እያደረገ ላለው ጉብኝትና ድጋፍ ከበዓሉ ጋር ተዳምሮ የተለየ ቀለምና ድምቀት እንዳለው ማስተጋባቱም ለውስጥም ለውጭም ዘርፈ ብዙ መልእክት እንዳለው መረዳት ይገባል። ከዚህም በላይ በዓላትን በደመቀ ሁኔታ ማክበሩ በሕዝባችን ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የራሱ አስተዋጽኦ አለው።
እነዚህ ኹነቶች በጦርነት የተጎዳው ሕዝባችን ወደነበረበት መደበኛ ሕይወት መመለስ እንደሚችል ተስፋ ይሰጣል። በመሆኑም በዓሉ በአግባቡ እንዲከበር በመንግሥት ትኩረት መሰጠቱ ተገቢ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
በአንድ በኩል ኅልውናችን ለማስከበር በሌላ በኩል የውስጥ ሰላማችንና ልማታችንን ለማፋጠን ኹላችንም እኩል ትኩረት ሰጥተን መንቀሳቀስ ቀጣዩ የትግላችን አቅጣጫ ነው። ትግል በአንድ ወቅት የሚጠናቀቅ ሳይሆን በየምዕራፉ
በቅብብሎሽ የሚቀጥል ጅረት ነው።
መጭው ጊዜ በተስፋ የሚጠበቅ የድል፤ የሰላምና የልማት ጊዜ ለማድረግ ኹላችንም በአንድነት እንረባረብ!
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/