
ላልይበላ፡ ታኅሣሥ 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምዕምናን በልበ ሙሉነት የልደት በዓልን በቅዱስ ላልይበላ እንዲያከብሩ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አብያተክርስቲያናትና ገዳማት አስተዳዳሪ አባ ፅጌ ሥላሴ መዝገቡ ጥሪ አቅርበዋል። አባ ፅጌ ሥላሴ መዝገቡ ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለቅዱስ ላል ይበላ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
አባ ፅጌ ሥላሴ የልደት በዓል በቅዱስ ላል ይበላ ማክበር ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑንም አንስተዋል። ❝እረኞች በአንድነት ሆነው የዓለም መድኃኒት ተወለደ ብለው እንደ አመሰገኑ ሁሉ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ ሊቃውንትም በጋራ ያመሰግናሉ❞ ነው ያሉት።
አካባቢው በችግር ውስጥ እንደነበር ያስታወሱት አባ ፅጌ ሥላሴ ሁላችንም በከባድ ሐዘን ውስጥ ነበርን ብለዋል። አሁን ግን ከወገናችን ጋር በዓሉን በተለመደው መልኩ ለማክበር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
❝በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ የተገኘ ክርስቶስ በተወለደበት በኢየሩሳሌም ይገኛል የሚል ቃል ኪዳን በተሰጠው ቅዱስ ሥፍራ ልደትን እንዲያከብሩ ለምዕምናን ጥሪ አቀርባለሁ❞ ነው ያሉት። የቤተክርስቲያኑ የተለመደው አገልግሎት ሳይጓደል እንደሚፈፀምም ገልፀዋል። ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ የጸጥታ ሥራ መሠራቱንም ተናግረዋል። ለዜጎች የየብስና የአየር ትራንስፖርት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ልደትን ለማክበር የሚመጡ ሁሉ ማሕደረ ቅርስ የሚባለውን ላስታን ተዘዋውረው እንዲገበኙም ለምዕመናን መልእክት አስተላልፈዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብም መንገድ የጠፋባቸውን በማመላከት፣ የደከሙትን በማሳረፍ፣ እግራቸውን በማጠብ፣ የሚችሉትን ከቤት በማሳረፍ የበረከት ሥራ እንዲሠሩም አሳስበዋል።
ከውጭ ሀገር የሚገቡ ኢትዮጵያውያን የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን እናውቃለን ያሉት አባ ፅጌ ሥላሴ ስለ ኢትዮጵያ የሚመሰክሩ ጀግኖች ናቸውም ብለዋል። አሁንም ሀገራቸውን ለማየትና የደረሰውን ጉዳት ለመመልከት የሚመጡ በመሆናቸው ለእነሱ ልዩ የሆነ አቀባበል አለንም ነው ያሉት።
ከውጭ ሀገር ለገቡት ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በልዩ ሁኔታ ከሁለት መቶ በላይ አስጎብኚዎች መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል። አስጎብኚዎቹ የቤተክስቲያኑን እና ወቅታዊ ሁኔታውን በሚገባ የሚያሥረዱ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። ሥጦታ በቤተክርስቲያኗ ተዘጋጅቶ እንኳን ደኅና መጣችሁ የሚል ልዩ የመቀበያ ቦታ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል። በሽብር ቡድኑ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሆቴሎች በእንግዶች የሚጎበኙ ኾነው ሌሎች ደግሞ እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ -ከላልይበላ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/