
ገንዳ ውኃ፡ ታኅሣሥ 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር በምዕራብ ጎንደር ዞን ከሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሀገሩን እየጠበቀ ለሚገኘው የፀጥታ ኀይል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምግብ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ምክትል ኀላፊ አቶ ነጻነት መንግሥቴ የሀገርን ሉዓላዊነት ላለማስደፈር እየተፋለመ ለሚገኘው የፀጥታ ኀይል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምግብ ነክ ድጋፍ አስረክበዋል።
ከአሁን በፊት በወልቃይት ግንባር ለሚገኘው የፀጥታ ኀይል ድጋፍ መደረጉን የገለጹት አቶ ነጻነት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን እስከ መጨረሻው #እስኪቀበር በሁሉም ግንባሮች የደጀንነት ተግባሩን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተናገሩት።
ድጋፉን የተረከቡት የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የዞኑ ጤና መምሪያ ኀላፊ ክሽን ወልዴ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ለፀጥታ ኀይሉ ያደረገው ድጋፍ ሠራዊቱን ይበልጥ የሚያበረታታና ለሚያደርገው የድል ግስጋሴ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የፀጥታ ኀይሉ የተቀናጀ እርምጃ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድንን የሀፍረት ካባ ያከናነበ መሆኑን የገለጹት ምክትል አስተዳዳሪዋ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
በድጋፍ ርክክቡ የተገኙት የዓባይ ክፍለ ጦር ስንቅና ንብረት እደላ ክፍል ኀላፊ ረዳት ሳጅን አለሙ በርሄ ኅብረተሰቡ ለፀጥታ ኃይሉ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሞራልና የትጥቅ ዝግጅቱን የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡-ቴዎድሮስ ደሴ-ገንዳ ውኃ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!