
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ግብሩ እና ሥራው ኹሉ ሰይጣናዊ ነው። የሽብር ቡድኑ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ድሃና ወረዳ ጭላ ቀበሌ በአንዲት ለፍቶ አዳሪ እናት ላይ የፈጸመው ግፍ እጅግ ከባድ ነው።
የችግሩ ሰለባ ወይዘሮ ግብጽ ቸኮለ ይባላሉ። የሽብር ቡድኑ በጭላ ቀበሌ እንደገባ አብዛኛው ጎረቤቶቻቸው ሸሽተዋል። እሷቸው ግን የአስራ አምስት ቀን አራስ ስለነበሩ እንደ መሸሸ አልቻሉም።
ታዲያ አንድ ቀን አካባቢው በሽብር ቡድኑ የጥይት ሩምታ ሲናጥ ወይዘሮ ግብጽ ባደረባቸው ፍራቻ ከአጠገባቸው ብቸኛ ከነበሩት ጎረቤታቸው ከአቶ ቢረስ ቤተሰብ ጋር ለመኾን ወሰኑ። አቶ ቢረስም “ቤት ለእግዚአብሄር” ብለው አራሷ አብረዋቸው እንዲኾኑ አደረጉ። ይኹን እንጂ የሽብር ቡድኑ አባላት አንድ ቀን ከሌሊቱ 7 ሰዓት ገዳማ ወደ አቶ ቢረስ ቤት በመሄድ እንዲከፍቱ ጠየቁ። በኀይልም በር ሰብረው በመግባት አቶ ቢረስን ጉሮሯቸውን አንቀው በመያዝ ገንዘብ እንዲሰጡ ጠየቁ። አቶ ቢረስም ከእጂ ወደ አፍ ኑሮ እንደሚኖሩና ገንዘብ እንደሌላቸው መለሱላቸው። የሽብር ቡድኑ በአቶ ቢረስ ላይ ብትራቸውን አሳረፉባቸው። አቶ ቢረስ ተማጸኑ፣ ለመኑ። የቡድኑ አባላት በአዛውንቱ ልመና ይበልጥ በመናደድ የዱላ ማዕት አወረዱባቸው።
ትንሽ ቆይተውም ከአቶ ቢረስ በእንግድነት ወደ ተጠጉት የአስራ አምስት ቀን አራስ እናት ፊታቸውን አዞሩ። ለመድፈር ሲሞክሩ አራሷ እናት አንድ ብልሃት በቅጽበት መጣላቸውና “የኤች አይቪ ተጠቂ ነኝ” አሏቸው።
በዚህን ጊዜ በጥላቻ የታወሩት የሽብር ቡድኑ አባላት ይህ የወለድሽው ልጅ አድጎ ነገ እኛን ነው የሚያጠፋው ብለው ህፃኑን በኀይል መሬት ላይ ጣሉት፤ ህፃኑም የሲቃ ድምጽ አሰምቶ አንድ ጎኑ ተገነጠለ፤ ወዲያውኑም ህይወቱ አለፈ። ህፃኑ ህይወቱ አልፎም በእግራቸው ደጋግመው በመርገጥ የጭክንናቸውን ጥግ አሳይተዋል። እናት በወቅቱም በድንጋጤ ራሳቸውን ስተው እንደነበር ነው የነገሩን። አሸባሪ ቡድኑ በእሳቸውና በአካባቢው ሕዝብ ከባድ ግፍ ማድረሱን ነው የነገሩን።
በአሸባሪ ቡድኑ የአማራ ጥላቻነት ልጃቸውን ያጡት ወይዘሮ ግብጽ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለማጥፋት የአማራ ሕዝብ እንቅልፍ ሊወስደው እንደማይገባ ተናግረዋል። የሽብር ቡድኑ አማራን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል ነው። በሕልውና ላይ የመጣን አጥፊ ቡድን ለማጥፋት የጋራ ትግል ስለሚጠይቅ በጋራ መነሳት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/