
ላልይበላ፡ ታኅሣሥ 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የልደት በዓልን በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ ለሚያከበሩ እንግዶች መስተንግዶውን የተሳካ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የላል ይበላ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ታላቁን በዓል ለማክበር ዝግጅት አድርጎ እንግዶችን እየተቀበለ መሆኑንም ገልጿል።
ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የላል ይበላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ማንደፍሮ ታደሰ የኢየሱስ ክርስቶስና የቅዱስ ወ ንጉሥ ላል ይበላ የልደት በዓል በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ በተለየ ድምቀት እንደሚከበር ገልፀዋል። ከተማ አስተዳደሩም ለዚሁ በዓል ለየት ያለ ዝግጅት አድርጓል ነው ያሉት።
ግብረ ኀይል በማቋቋም ወደ ሥራ መገባቱንም ገልፀዋል። ሆቴሎች እንግዶችን በመልካም መስተንግዶ ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የባንክ እና ሌሎች አገልግሎቶች መጀመራቸውንም ጠቅሰዋል።
የእንግዶች ሰላም የተጠበቀ እንዲሆን ሁሉን አቀፍ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።
በአሸባሪው ቡድን ጉዳት የደረሰበት የላል ይበላ አየር ማረፊያ የአካባቢውን ቱሪዝም ለማነቃቃት መንግሥት ባደረገው ልዩ ትኩረት ሥራ እንዲጀመር መደረጉንም አስታውቀዋል።
ከደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት በተጨማሪ በዙሪያው ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆን መሠራቱንም አስታውቀዋል።
እንግዶች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ተረድተው ሳይሰጉ ወደ ላል ይበላ መጥተው በዓሉን እንዲያከብሩም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/