“አጼ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ክብር እና ስልጣኔ እራሳቸዉን አሳልፈዉ የሰጡ በመሆናቸዉ ታሪካቸዉን ማወቅ እና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ፈለጋቸዉን ልንከተል ይገባል” የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር

252

አዲስ አበባ፡ ታኅሣሥ 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዞች ተወስደው እና ከ150 ዓመታት በኃላ እንዲመለሱ የተደረጉት የአጼ ቴዎድሮስ ሽሩባ እና የመቅደላ ቅርሶች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ወደ ጎንደር ከተማ በክብር ዛሬ ጥዋት ተሸኝተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ከፍታ ሲታትሩ የነበሩት ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ጠላት ኢትዮጵያን ለመውረር ሲሞክር በጀግንነት ተፋልመዋል ያሉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በመጨረሻም መቅደላ ላይ በሀገር ዉስጥ ባንዳዎች መሪነት በእንግሊዞች እንዲያዙ ሙከራ ሲደረግ እጀን ለጠላት አልሰጥም በማለት ሚያዚያ 7/1860 ዓ.ም የያዙትን ሽጉጥ ጠጥተዉ ለሀገር እና ለሕዝብ ሲሉ ተሰዉተዋል ነው ያሉት፡፡

ንጉሡን በሕይዎት መያዝ ያልቻሉት እንግሊዞች የአጼ ቴዎድሮስን ሽሩባ እና በተለያዩ ጊዜያት አጼ ቴዎድሮስ ከጠላት ጋር የተፋለሙባቸዉን ባህላዊ የጦር መሳሪያዎች እና በመቅደላ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ወስደዉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ አቶ አገኘሁ ከ150 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቅረስ አስመላሽ ኮሚቴ አማካኝነት እንዲመለሱ ተደርገዋል ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ተቀምጠው የነበሩት እነዚህ ታሪካዊ ቅርሶች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባት አርበኞች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ወደ ቦሌ አዉሮፕላን ማረፊያ፤ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር አጼ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ክብር እና ስልጣኔ እራሳቸዉን አሳልፈዉ ሰጥተዋል፤ ታሪካቸዉን ልናቅ ብቻ ሳይሆን ፈለጋቸዉን ልንከተል ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ የኖሩ መሪ እንደነበሩ አውስተው የተዘረፉት ቅርሶች ታሪካዊ ብቻ ሳይሆኑ የታሪክ ምልክት፣ የመስዋእትነት ውርስ እና የአንድነታችን ዓርማ በመሆናቸው በአግባቡ ልንጠብቃቸዉ ይገባል ብለዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ አማረ መስፍን አጼ ቴዎድሮስ ለሀገር ኑሮ ለሀገር መሞትን አስተምረውን አልፈዋል ብለዋል፡፡ የአሁኑ ትውልድም አንድነቱን በማጠናከር የሀገር ውስጥ ባንዳን እና የውጭ ጠላቶችን መመከት ይገበዋል ነው ያሉት፡፡ በጎንደር ከተማ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በአጼ ቴዎድሮስ ሽሩባ ፊት ኢትዮያዊነትን እናደምቀበታለን ብለዋል፡፡

ዘጋቢ:–በለጠ ታረቀኝ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የልማት ፍላጎትን ለማሟላትና መንግሥታዊ አገልግሎትን ለማሳደግ የገቢ ተቋም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር)
Next articleለሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ የተሽከርካሪ ስጦታ ተበረከተላቸው።