የግዮን በዓልን በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስታወቀ፡፡

246

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የግዮን በዓል በየዓመቱ ጥር 13 በምዕራብ ጎጃም ዞን ሠከላ ወረዳ የታላቁ ዓባይ ወንዝ መነሻ በሆነችው ግሽ ዓባይ ከተማ ከአቡነ ዘርዓ ብሩክ ዓመታዊ የንግሥ በዓል ጋር በድምቀት ይከበራል፡፡ በሰከላ ወረዳ የታላቁ ዓባይ ወንዝ መነሻ ምንጭ፣ ግሺ ተራራ፣ የጉደራ ሐይቅ፣ አርሲታ ዋሻ፣ የፋሲል ግንብ (የአባ ግፍ ጅምር ግንብ)፣ ትክል ድንጋዮች፣ የአላዛር ዋሻ፣ ድንጋይ ቀዳዳ እና ሌሎች የመስህብ ሃብቶች ይጎበኛሉ፡፡

በመጪው ጥር 13 ለአራተኛ ጊዜ ለሚከበረው የግዮን በዓል ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዓሉ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት የሚከበር ሲሆን ለዚህም በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ አስታውቀዋል፡፡ አቶ መልካሙ ምዕራብ ጎጃም ዞን የበርካታ የተፈጥሮ እና ሠው ሠራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዲያስፖራዎች እና የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች በቦታው ተገኝተው የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

አቶ መልካሙ ዓባይ የአንድነት እና የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት፣ የአብሮነታችን እና የጥንካሬያችን ማሳያም ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ አስተማማኝ ሠላም መኖሩን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው እንግዶችን ለመቀበል ሕዝቡም ሆነ የፀጥታ ኀይሉ ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡

ዞኑ ከተፈጥሮና ሠው ሠራሽ የቱሪዝም መዳረሻ በተጨማሪ መልማት የሚችል ለም መሬት፣ ዓባይን ጨምሮ ክረምት ከበጋ ሳያቋርጡ የሚፈሱ ወንዞች የሚገኙበት፣ ታታሪ እና ሥራ ወዳድ ሕዝብ ባለቤት በመሆኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሠማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡
አቶ መልካሙ ሕዝቡም በህልውና ዘመቻው ያሳየውን አንድነት እና መተባበር በበዓሉ አከባበር ላይ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleሕብረ ብሔራዊቷን ኢትዮጵያ የማጽናት እና የመጠበቅ አደራ ተብሲር –የንጉሱ ሽሩባ!
Next article“የመይሳው ሥሬት የካሳ ቁንዳላ፣ የአንድነት ገመድ ነው ውሉ የማይላላ”