
ታኅሣሥ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደራል ተቋማትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲያካሂዱ የነበረውን ውይይት አጠናቀቁ።
በዘመቻ ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት በተገኙ ድሎች፣ በታዩ ውስንነቶችና በቀጣይ ስለሚኖረዉ አቅጣጫ ለሦስት ቀናት ውይይት ሲካሄድበት የቆየው የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ግምገማዊ ሥልጠና ዛሬ ተጠናቋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በውይይታቸው በጦርነት የሚገኝ ድልን በአግባቡ መምራት ከጦርነቱ በኋላ ለሚመጣ መረጋጋትና ሰላም እንዲሁም ለዘላቂ የሀገር ግንባታ ሂደት ትልቅ ፋይዳ እንዳለዉ አስምረውበታል፡፡
በዘመቻውም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ድል ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የህልውና ዘመቻው ያስከተለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እጅግ አሳዛኝና የሀገር እዳ ቢሆንም ሂደቱ ግን በርካታ ትሩፋቶችን እንዳስገኘ አመራሩ መገምገሙ ተመልክቷል፡፡
ተናቦና ተቀናጅቶ በአንድ አመራር ለአንድ ዓላማ የመሥራት አቅም፣ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትና ሁለንተናዊ ሕዝባዊ ተሳትፎና ተደጋግፎ ችግሮችን በጋራ መሻገርን እንዳስገኘ አመራሮቹ ማረጋገጣቸው ተመልክቷል፡፡
አመራሮቹ ከድሎቹ ጋር የታዩና ቀጠይም ሊኖሩ ስለሚችሉ መልካም እድሎችና ዝንፈቶችን በትኩረት ገምግመዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የመጀመሪያው ምእራፍ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኢትዮጵያዊያን የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸው ለዚህም ላቅ ያለ ተሳትፎና አበርክቶ ምስጋና አቅርበዋል።
በተገኘው ድል ሳንኩራራ በቀጣይ ሊያጋጥሙን ለሚችሉ ፈተናዎች ተግተን መዘጋጀት እንደሚገባንም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶች ለመጠገን የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስምረውበታል፡፡
በየደረጃዉ ያለው አመራርም በጦርነቱ ጫና የደረሰበትን የብልፅግና ጉዟችንን ለማስቀጠል ታሪካዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡
“ኢትዮጵያዊያን በዘመቻው የተገኘውን የኅብረ ብሔራዊ አንድነት ስሜት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባትና ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ እንድንጠቀምበት ጥሪ አቀርባለሁ” ማለታቸውን ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
