❝የልደት በዓል በብሔራዊ ደረጃ በላልይበላ ይከበራል❞ የቱሪዝም ሚኒስቴር

122

ታኅሣሥ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዘንድሮዉ የልደት በዓል በልዩ ድምቀት በብሔራዊ ደረጃ በላልይበላ ከተማ እንደሚከበር የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ከአማራ ክልል መንግሥት፣ ቱሪዝም ቢሮ እና ከደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

በላልይበላ ከተማ የሚከበረው የልደት በዓል እንደሀገር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና በፀጥታ ችግር ተቀዛቅዞ የነበረዉን የቱሪዝም ዘርፍ ልማት እንቅስቃሴ እንደሚያነቃቃው ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገሪቱን ጥሪ ተቀብለው የመጡ የዳያስፖራ አባላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የመገናኛ ብዙኀን ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ኢትዮጵያ የምትገነባው በዕውቀት ማዕከላት ውስጥ ነው!❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር)
Next articleአመራሩ በተገኘው ድል ሳይኩራራ በቀጣይ ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ፈተናዎች እንዲዘጋጅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አሳሰቡ።