
ሰቆጣ፡ ታኅሣሥ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚሊሻ በአንድ እጁ ነፍጥ ይዞ ጠላትን፣ በአንድ እጁ ደግሞ ማረሻ ይዞ ድህነትን ተፋልሟል፤ እየተፋለመም ይገኛል። ሀገሪቱ የውስጥ እና የውጭ ጠላት በወረራት ጊዜ የሀገሩን ክብር በማስቀደም በጀግንነት በመፋለም የማይደበዝዝ ደማቅ ታሪክ ጽፏል፤ እየጻፈም ይገኛል። ይሕንን ሲያደርግ ደግሞ በመንግሥት ደመወዝ እየተከፈለው አይደለም፤ ስንቁን ከደጀን ሕዝቡ፣ ክብሩ እና ነፃነቱን ደግሞ ደመወዙ አድርጎ እንጂ።
አሁን ላይም በኅልውና ዘመቻው ከየአካባቢው በመሰባሰብ ተፋልሟል፤ አኩሪ ድልም አስመዝግቧል። ሀገር ወደ ሰላም ስትመለስ ደግሞ ወደ ቀየው ተመልሶ በግብርና ሥራው ድህነትን ለመፋለም ተዘጋጅቷል።

ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ በለሳ ሀገራቸውን ከወራሪው ለመከላከል በግንባር ከተሰለፉት መካከል አቶ አራጋው ነጋሽ አንዱ ናቸው። አቶ አራጋው እንዳሉት በዋግ ግንባር በተካሔደው ውጊያ ጀግኖቹ የሚሊሻ አባላት ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ የሽብር ቡድኑን ደምስሰዋል። ከቀውዝባ እስከ ሰቆጣ በነበረው ትግልም የሽብር ቡድኑን እያሳደዱ ለቅመውታል። የተረፈውም ፈርጥጧል ነው ያሉት።
ሌላኛው አቶ ማስረሻ ሙጬም በተካሔደው የኅልውና ዘመቻ ከመሳሪያ ባለፈ በመንጋ ከመጣው ወራሪ ጋር እጅ በእጅ በመተናነቅ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠላትን በመደምሰስ ጀብዱ ፈጽመዋል። የደጀኑ ሕዝብ ከሚያደርገው የስንቅ አቅርቦት ባለፈ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ እና ንብረታቸውን በመጠበቅ ያከናወነው ተግባር ለትግሉ ትልቅ አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል። “ለጠላትም፣ ለችግርም እጅ አንሰጥም፤ እያመረትን ድህነትን፣ እየተዋጋን ጠላትን እናሸንፋለን” ብለዋል፡፡ ጠላት እስከመጨረሻው ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከጎንደር ዙሪያ ወረዳ የዘመቱት ታያቸው ተስፋ እንዳሉት ከድሃና እስከ ቀውዝባ በነበረው ተጋድሎ የሚሊሻ አባላቱ ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት በጠላት ላይ ከፍተኛ ጀብዱ ፈጽመዋል። ሕዝቡም በምግብ አቅርቦት እና የዘማች ሰብልን በመሰብሰብ ያደረገው ድጋፍ ወኔ እንደሆናቸው ተናግረዋል።
በቀጣይም አካባቢን በመጠበቅና በልማት ሥራቸው ድህነትን ለመዋጋት ቆርጠው መነሳታቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት የሥልጠና ከፍተኛ ባለሙያ ባሕሩ ደምሌ እንዳሉት በዋግ ግንባር የሚሊሻ አባላቱ ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት ጀብዱ ፈጽመዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብም በስንቅ አቅርቦት እና የዘማች ሚሊሻ አባላትን ሰብል በመሰብሰብ፣ የተጎዳን በመንከባከብ ደጀንነቱን በተግባር መፈጸሙን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ-ከሰቆጣ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/
