በራያ ቆቦ ወረዳ በሚገኘው የሮቢት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ 19 የተናጠልና የጅምላ መቃብሮች ተገኙ።

437

ታኅሣሥ 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የራያ ቆቦ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ በላይነጋ እንደገለጹት በሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከተገኙት 19 መቃብሮች 3ቱ በእያንዳንዳቸው እስከ 30 ሰዎች የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች ናቸው።

ወራሪው ቡድን የወረዳውን ትምህርት ጽሕፈት ቤት እና በወረዳው የሚገኙ 7 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 129 ትምህርት ቤቶችን በመውረር ዘረፋ መፈጸሙንና ንብረቶችን ማውደሙን ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ ከዘረፋቸውና ካወደማቸው ንብረቶችና ቁሳቁሶች መካከልም የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕላዝማዎች፣ የተማሪ ሰነዶችና ሌሎችም የትምህርት ቤቱ ንብረቶች ይገኙበታል።

የሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጥበቃ ሠራተኞች አቶ ይመር አየለ እና ዝናቡ ሰማው ወራሪው ቡድን ትምህርት ቤቱን የመቃብር ስፍራ እንዳደረገው ገልጸዋል።

የሮቢት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከ1ሺ 800 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምር እንደነበር መገለጹን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል ለተፈናቀሉ እና በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
Next articleጎንደር ለእንግዶቿ ንጉሣዊ አቀባበል ለማድረግ ሽር ጉድ እያለች ነው፡፡