የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በአስተዳደር ወሰን፣ ማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ሀገር አቀፍ ጥናት ማከናወኑን አስታወቀ።

478

አዲስ አበባ፡ ታኅሣሥ 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሚሽኑ ከ2012 መጨረሻ ጀምሮ ሀገር አቀፍ ጥናት እና ምርምር ሲያከናውን መቆየቱን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

በዜጎች መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ሲያደርግ የቆየውን የወሰንና የማንነት ጥያቄ ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በኅብረተሰቡ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸውን እና ገለልተኛ የሆኑ ምሁራንን በኮሚሽኑ አዋቅሮ ሲሠራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ኮሚሽኑ ከሕዝብ እና መንግሥት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን የገለጹት የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ጣሰው ገብሬ (ዶ.ር) ከ2012 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ከትግራይ ክልል ውጪ በ68 ልዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ላይ ጥናት ሲያከናውን መቆየቱን ነው የገለጹት፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናቱን በባለቤትነት ይዞ ሲመራ መቆየቱን እና ሌሎች የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ያሉ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጥናቱ ላይ ተሳታፊ ሆነው ሲሠሩ እንደቆዩም አንስተዋል፡፡

በጥናቱ በርካታ ምክረ ሐሳቦች የቀረቡ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወል ሁሴን በግኝቶቹ መሰረት በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ይደረግበታልም ነው ያሉት፡፡

ሀገር አቀፉ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ኮሚሽን ጥናት እና ምርምር ከውይይት በኋላ የጥናት እና ምርምር ምክረ ሐሳብን ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ተገልጿል።

ዘጋቢ፡-አየለ መስፍን-ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝የተለየ ሐሳብ ያለው ኢትዮጵያዊ ሐሳቡን የሚቀበል ሥርዓት አጥቶ ጫካ የሚገባበት ጊዜ መቆም አለበት❞ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
Next article“ሐሰን ከረሙ የቆላው መብረቅ፣ ጎራ ለጎራ አባሮ እማይለቅ”