
ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪዎቹ የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ሸኔ የፈጸሙትን ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ውድመት የሚያሳይ ድረ ገጽ ይፋ
ተደርጓል።
አሸባሪዎቹ የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ሸኔ የፈጸሟቸውን እጅግ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የመሰረተ ልማትና ንብረት ውድመቶች እንዲሁም ወንጀሎችን በፎቶ ማስረጃነት የሚያሳይ https://nomore-ethiopia.org/ የተባለ ድረገጽ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይፋ አድርገዋል።
ድረገጹ ስያሜውን ያገኘው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ግንዛቤዎችንና ለውጦችን የፈጠረውን የ#በቃ ወይም #Nomore እንቅስቃሴን ተከትሎ ሲሆን ንቅናቄው አፍሪካውያንና ሌሎችንም ያነሳሳ እንደሆነ ተመልክቷል።
ከዚህ ባለፈም አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኀን በኢትዮጵያ ላይ እያሰራጩት ስላለው ሐሰተኛ መረጃ እና አንዳንድ የምእራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱት የኢኮኖሚ ጦርነት፣ የዲፕሎማሲ ፕሮፖጋንዳ እንዲሁም በኢትዮጵያ በአጠቃላይም በአፍሪካ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ለመቃወም ያለመ ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
