የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው።

221

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ጀምረዋል፡፡ ለ3 ቀናት የሚቆየው ውይይትም የተገኙትን ሁለንተናዊ ድሎች ጠብቆ የማስፋትና ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማሸጋገር ላይ ያተኮረ ይሆናል ተብሏል፡፡
የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔሃብታዊ፣ ሰብዓዊና የፀጥታ ፈተናዎችን በብቃት መፍታትና በአግባቡ መምራትም እኩል ትኩረት ያገኛሉ ነው ያለው፡፡

‹‹በኅልውና ጦርነት ሂደት ውስጥ ያገኘናቸውን ሀገራዊ አንድነት፣ ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራት ልምድ፣ በጋራ ዓላማ ለጋራ የመስራት ልምድ፣ የአመራር ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቁርጠኝነት ለሀገራችን ዘላቂ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ የመምራት አስፈላጊነት ላይ ከፍተኛ አመራሩ በጥልቀት ይወያያል›› ተብሏል፡፡

በውይይቱ የድኅረ ጦርነት ፖለቲካዊ፣ ምጣኔሃብታዊ፣ የፀጥታና ሰብዓዊ ሁኔታዎች በብቃት በመምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎም እንደሚጠበቅ ነው ከብልፅግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ የሚጠቁመው፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበሽብር ቡድኑ የወደሙ የጤና ተቋማት ቀደም ብሎ ይሰጡት ከነበረው አገልግሎት በተሻለ መልኩ ሕዝብን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ገለጸ።
Next article“ከድል በኋላ ያሉ ድኅረ ድል መዛነፎችን ማረም እና የጋራ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ ነው” አቶ ተመሥገን ጥሩነህ