
ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2012 ዓ/ም (አብመድ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መሠረት በመስከረም ወር የመጨረሻው ሰኞ ሥራ ይጀምራል፡፡ በዚህም መሠረት ነገ መስከረም 26 ቀን 2012ዓ.ም የ5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት ሥራውን በይፋ ይጀምራል፡፡
የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና አፈ ጉባኤዎች በተገኙበት በኢፌዴሪ ፕረዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ንግግር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ግለሰቦችም በመክፈቻ መርሀ ግብሩ እንደሚገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡