እንግዶችን ለመቀበል በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

215

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ”አንድ ሚሊየን ዲያስፖራ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው፡፡ እንግዶቹን ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተቀብሎ ለማስተናገድ በቂ የፀጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቅድመ ዝግጀቱን እና በዝግጅቱ የሚኖሩትን መርሐ ግብሮች አስመልክቶ ትናንት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኅላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ በክልሉ የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ከፌዴራል መንግስት እና ከክልሉ የፀጥታ ኀይሎች ጋር በጋራ በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት ቢሮ ኅላፊው እንግዶች ያለምንም ስጋት በዓሉን በሀገራቸው ያሳልፋሉ ነው ያሉት፡፡
በመርሐ ግብሩ “ልደትን በላል ይበላ” እና “ጥምቀትን በጎንደር” ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ያሉት አቶ ጣሂር ከጸጥታ ኅይሎች በተጨማሪ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ተጨማሪ ጉልበት ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡ ኅላፊው የአማራ ሕዝብ በየአካባቢው ወገኖቻቸውን በተለመደው የእንግዳ ተቀባይነት ባህል በመቀበል እንዲያስተናግዱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ወርሯቸው በነበሩ በርካታ አካባቢዎች የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በማውደሙ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ለመስራት ጥረት መደረጉን ያወሱት ኅላፊው የኤሌክትሪክ ኃይል እና ሌሎች አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት በፍጥነት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በቀሪ ጊዜያት ባለሃብቶች፣ የክልሉ ሕዝብ አጋሮች እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሌሎቹን የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት መልሶ ግንባታ በማፋጠን ለእንግዶች ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩም አቶ ጣሂር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleየጦላይ የከፍተኛ ባለ ሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሰልጣኝ ምልምል ወታደሮችን የሥልጠና ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት አካሄደ፡፡
Next article“በቆይታችሁ የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም የፍትሕ አደባባይ የሚገልጽ የዲፕሎማሲ ስንቅ ታገኙበታላችሁ” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን