በአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ አካሄዱ፡፡

291

ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2012 ዓ/ም (አብመድ) በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና የሃይማኖት አባቶች ሰልፍ አካሄዱ፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ እና በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአበርገሌ ወረዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች እና የሃይማኖቱ መሪዎች ‹‹በቤተ ክርስቲያን እና በምዕመኖቿ ላይ የሚደርስ ጥቃት ሊያበቃ ይገባል›› ሲሉ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

በሰልፉ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ይቁም፤ ንዋየ ቅድሳትን፣ አገልጋዮችና ምዕመናን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች ይቁሙ›› የሚሉ መልዕክቶች ተላልፏልዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ሺህ ዘመናት ፊደልን ያስቆጠረች፣ ወንጌልን ያስተማረች፣ አገርን ያሰከበረች በመሆኗ ምሥጋና እንጂ ጥቃት አይገባትም›› የሚሉ መልዕክቶችም በሰልፎቹ ተስተጋብተዋል፡፡

በተመሳሳይ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በአነደድ፣ ደባይ ጥላት ግን፣ መርጡለ ማርያም፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ፣ በምዕራብ ጎጃም ሰሜን አቸፈር፣ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳዎች ሰልፎች ተካሂደዋል፤ ተመሳሳይ መልዕክቶችም ተስተጋብተዋል፡፡

በየማነብርሃን ጌታቸው

መረጃው የየወረዳዎቹ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤቶች ነው፡፡

Previous articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ነገ ይጀምራል፡፡
Next articleጎንደር አካባቢ ተከስቶ የነበረው ችግር የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች ተናገሩ፡፡