የጦላይ የከፍተኛ ባለ ሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሰልጣኝ ምልምል ወታደሮችን የሥልጠና ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት አካሄደ፡፡

397

ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጦላይ የከፍተኛ ባለ ሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለአራተኛ ጊዜ የተቀበላቸውን ሰልጣኝ ምልምል ወታደሮች የሥልጠና ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል፡፡
የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዱኛ ኢትቻ እንደተናገሩት አባትና እናታችሁ ብሎም የሀገር ሽማግሌዎች መርቀው ወደ ማሰልጠኛ ሲልኳችሁ ሰልጥናችሁ የሀገራችሁን ሰንደቅ ዓላማ በጀግንነት ከፍ አድርጋችሁ እንድታውለበልቡ በአደራ ጭምር ነው።
በቀጣይ የሚሰጣችሁን ስልጠና በንቃት መከታተል ይገባችኋል ብለዋል።

የወታደር ልጆች የሆኑት ሰልጣኝ ምልምል ወታደር ዳዊት አንዳርጌ እና ምልምል ወታደር አብርሃም አንዳርጌ ስልጠናቸውን በሚገባ በመከታተል ከጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጋር ተቀላቅለው የሀገራቸውን ሉዓላዊነት እንደሚያስከብሩ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleከጥንታዊቷ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ በተለያየ ዘርፍ ለተጉ የሀገር ባለውለታዎች “የአጼዎቹ” ሽልማት ይበረከታል፡፡
Next articleእንግዶችን ለመቀበል በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡