
ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዳያስፖራው የተለያዩ መረጃዎችን የሚያገኝበት አዲስ የዳያስፖራ ማዕከል ወደ ሥራ ገባ።
ማዕከሉን ወደ ሥራ የማስገባት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። በሥነሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የዳያስፖራ ተወካዮች ተገኝተዋል።
ማዕከሉ የበዓል ቀናትን ጨምሮ ከእሁድ እስከ እሁድ አገልግሎት ይሰጣል። በኢኮኖሚው መስክ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የተመለከቱ መረጃዎችን ለዳያስፖራው ተደራሽ የሚያደርግ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ማኅበራዊ ኑሮን የሚያሻሽሉ ሥራዎችን በተመለከተ መረጃዎች የሚያገኙበት ሥርዓት መዘርጋቱንም ለማወቅ ተችሏል።
በማዕከሉ የአንድ መስኮት አገልግሎት ይሰጣል፤ ወሳኝ ኩነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎትም ዳያስፖራው የሚያገኝ ይሆናል።
ዳያስፖራውን በተመለከተ ስለተዘጋጁ ልዩ ልዩ ኹነቶችም በማዕከሉ ገለፃ ይደረጋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
