
ባሕርዳር፡ ታኅሣሥ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሚሽኑ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን እና የሚደገፉበትን ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የኮሚሽኑ የሕዝ ግንኙነት ኀላፊ እያሱ መስፍን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል 2 ነጥብ 3 ሚሊዬን ዜጎችን ከቀያቸው እንዲሰደዱ አድርጓል ብለዋል። ኮሚሽኑ በመጀመሪያ ደረጃ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመቀበል ሰብዓዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንም አስረድተዋል። ተፈናቃዮች ምግብ፣ ነፃ የጤና አገልግሎት እና ንፁህ የመጠጥ ውኃ እንዲያገኙ ተደርጓል ነው ያሉት። የሽብር ቡድኑ የሽንፈት ካባ ተከናንቦ ወርሮ የያዛቸው አካባቢዎች ነጻ በመሆናቸው ኮሚሽኑ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስና የመደገፍ ተግባሩን አጠናክሮ እንደቀጠለ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው አስረድተዋል። እስካሁን ከ328 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በመንግሥት ድጋፍ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውንም ገልጸዋል።
በርካታ ተፈናቃዮች በራሳቸው ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የጠቀሱት አቶ እያሱ ከመጪው የልደት በዓል በፊት ቀሪ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ ብለዋል። በአማራ ክልል የሚገኙ ሁሉም የመጠለያ ጣቢያዎች ከልደት በዓል በኋላ ይዘጋሉም ብለዋል።
ነፃ በወጡ አካባቢዎች ጠላት ሙሉ በሙሉ ውድመት በመፈጸሙ በወር 1 ነጥብ 2 ሚሊዬን ኩንታ እህል ለ11 ነጥብ 4 ሚሊዬን ሕዝብ ድጋፍ ያስፈልጋል ነው ያሉት። አቶ እያሱ መላው ሕዝብ ለዘመቻው ርብርብ እንዲያደርግ እና ሁሉም ተጎጂዎች ሙሉ በሙሉ እስኪቋቋሙ ድረስ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።
እስካሁን 602 ሺህ 750 ኩንታል እህል ለተፈናቃዮች መድረሱን የጠቆሙት ኀላፊው በዚህም የ 3 ሚሊዬን 795 ሺህ 302 ዜጎችን ሕይወት መታደግ መቻሉን ገልጸዋል። አቶ እያሱ ከወለጋ የተፈናቀሉ ዜጎችም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
