
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ 67 ሠላማዊ ሰዎችን በግፍ መጨፍጨፋቸውንና 12 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደተፈጸመባቸው የዞኑ አስተዳዳር ገልጿል፡፡
በዞኑ አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈጸመበት ወቅት 6 ሆስፒታሎችና ከ180 በላይ ትምህርት ቤቶችን አውድሟል፤ ዘርፏል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረጻድቅ በሰጡት መግለጫ አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ተቀናጅተው በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ንጹሃንን በግፍ መጨፍጨፋቸውን አመልክተዋል።
የህወሓት ወራሪ ንጹሃንን ከመጨፍጨፋም ባለፈ የጤና፣ የትምህርትና መሰል ተቋማትና መሰረተ ልማቶችንም አውድሟል ብለዋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ሕዝብ ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር አሸባሪዎቹን ከአካባቢው መደምሰሱን ገልጸው፤ በጥቃቱ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን የማቋቋም ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ በሰሜን ሸዋ ዞን አምስት ወረዳዎች ላይ ከፍተውት በነበረው ጥቃት የበርካቶችን ህይወት መቅጠፋቸውን አስታውቀዋል።
የተጎጂ ቤተሰቦችንና የተፈናቀሉትን ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ መላው ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እንዲያደርጉ አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
