አካባቢያቸውን በጠላት ላለማስደፈር በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ በምዕራብ ጎንደር ዞን የሚገኙ የወገን ጦር አባላት ገለጹ።

300

ገንዳውኃ፡ ታኅሣሥ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራና በአፋር ክልል በርካታ ንጹሐንን ገድሏል፣ ንብረት ዘርፏል፤ አውድሟል፡፡ የወገን ጥምር ጦር በጥፋት ቡድኑ ላይ በወሰደው የተቀናጀ እርምጃ አብዛኛው ሙት፣ ቁስለኛ እና ምርኮኛ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ፈርጥጧል። የሞት ጽዋ የናፈቀው ወራሪው ቡድን እና ግብረ አበሮቹ በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ቦታዎች ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን ቢፈጽምም የወገን ጦር ከሕዝብ ጋር በመቀናጀት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ተገኝቶ ከጠላት የሚመጣ ጥቃትን ለመቀልበስ በተጠንቀቅ ላይ የሚገኙ የወገን ጦር አባላትን አነጋግሯል። የወገን ጦር አባል ሰለሞን መዝሙር እና ማሩ በርሄ አሸባሪውን ቡድን እና ግብረ አበሮቹን ግብዓተ መሬት ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላኛው የወገን ጦር አባል ሙሉነህ ጥሩነህ ሕዝቡ ተረጋግቶ እንዲኖር እና የልማት ሥራውን እንዲከውን ጊዜው የሚጠይቀውን ሀገራዊ ግዳጅ እየተወጡ መሆኑን ገልጿል። አካባቢያቸውን በጠላት ላለማስደፈር በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡
የወገን ጦር አባል መሰረት ባዬ በበኩሏ የሀገሪቱ ሰላም እስኪረጋገጥ ድረስ የሚጠበቅባትን እንደምትወጣ ተናግራለች፡፡
ሽንፋን ለመውረር የመጣውን የሽብር ቡድን ላይመለስ እንዳሰናበቱት የገለጹት የወገን ጦር አባላቱ የሀገር ሉዓላዊነት እና የዜጎች ነፃነት በክንዳቸው ሳያረጋግጡ ወደ ቤት እንደማይመለሱ ገልጸዋል። ለሕዝብ እና ለሀገር ሲባልም በአስፈላጊው ጊዜ እና ቦታ አስፈላጊውን ጀብድ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ነው የወገን ጦር አባላቱ ያረጋገጡት።
ዘጋቢ፡-ቴዎድሮስ ደሴ-ከቋራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleአነጣጥሮ ተኳሽ ጀግና የምትወዱ ከእነ አጅሮች ሀገር ራያ ውረዱ”
Next article“በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ድርሻ የሌለው ኢትዮጵያዊ የለም” ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት