“እናቱን የበላውን ከሃዲ ቡድን ጨርሶ መቅበር ይገባል” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ጀግኖች

382

ሁመራ፡ ታኅሣሥ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምድሩ እጅግ ለም፤ ሕዝቡ ለጠላት ማይቀመስ ጀግና ነው፤ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ ሪ ቡድን በሥልጣን ዘመኑ ይህንን አካባቢ ያለማንነቱ ማንነት ሰጥቶ ሃብቱን ሲዘርፍ፣ ሲገድል እና ሲያፈናቅል ቆይቷል፡፡ ለጠላቱ የእግር እሳት የሆነው የወልቃይት አማራ “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” ብሎ የትግል አጋሮቹን ከጎኑ አሰልፎ ሥልጣኑን ሁሉ ጠቅሎ ይዞ ያሻውን ሲያደርግ ከነበረ ማፈያ አሸባሪ ቡድን ጋር እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ አድርጓል፡፡ ድል ምንግዜም ከእውነት ጋር ናት እና አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዳግም የወልቃይት ምድርን ላይረግጥ ተንኮታኩቶ ተባረረ፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሚሊሻ ዋኘው ተስፋዬ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ በአሸባሪው ትህነግ ግፍ የተፈጸመበት በመሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ በሱዳን በመሸጉ ጀሌዎቹ እና ከትግራይ ክልል በሚነሱ አሸባሪዎቹ ተደጋጋሚ ጥቃት ቢያደርግም ጀግናው የወልቃይት ሕዝብ ከፀጥታ ኀይሉ ጋር ተቀናጅቶ አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው ነው ብለዋል::

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ክህደት ፈጽሞ ሲደመሰስ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፀጥታ ኀይሉ ጋር በመሆን የሚሸሸውን የሽብር ቡድን መደምሰሱን ነው አስተያየት ሰጪው ያስታወሱት፡፡

ሌላኛው ሚሊሻ ብርሃኔ ጌታሁን ቤቴን፣ ንብረቴን እና ቤተሰቤን ሳይሉ ይህንን ሀገር አፍራሽ አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመቅበር ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ዘመቻ እንደወጡ ነግረውናል፡፡ አስተያየት ሰጪው አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ የፈጸመው ክህደት ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት እንደነበር ገልጸዋል። እናቱን የበላውን ከሃዲ ቡድን ጨርሶ መቅበር ይገባልም ነው ያሉት፡፡ የወልቃይት ሕዝብ አሁንም ከፀጥታ ኀይሉ ጋር በመሆን ሀገሩን ከዚህ አሸባሪ እና ከሃዲ ቡድን ለመታደግ በንቃት እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ እነሱም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከምድረ ገጽ ካልጠፋ ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንደማይመለሱ ቃል ገብተው ከቤት መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላው አሚኮ ያነጋገራቸው እና ሰላም ብለው የሰየሙትን የሚሊሻ ኀይል ሲያስተባብሩ ያገኘናቸው ሚሊሻ አጋለሽ ታደገ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን በሥልጣን ዘመኑ ጭምር ይታገሉት እንደነበር ገልጸው አሸባሪው ቡድን የወልቃይት ጠገዴን ምድር ዳግም አያስባትም ነው ያሉት፡፡ የሽብር ቡድኑ ወደ ሱዳን ለመፈርጠጥ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ሕዝቡ እና የፀጥታ ኀይሉ በቅንጅት እየደመሰሱት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሀገር ብሎም በሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ ሊያበቃ እንደሚገባ በመግለጽ ለዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊ አምርሮ በመታገል ሊቀብረው ይገባል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- የማነብርሃን ጌታቸው

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተልጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleበአሸባሪው ትህነግ የወደመው የአለውሃ ድልድይ የግንባታ ሥራ ተጀመረ።
Next articleአነጣጥሮ ተኳሽ ጀግና የምትወዱ ከእነ አጅሮች ሀገር ራያ ውረዱ”