አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 11ዱ ሥራ ጀመሩ።

115

ታኅሣሥ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በኮምቦልቻ ከተማ ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 11ዱ ምርት ማምረት መጀመራቸውን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

አሸባሪ ቡድኑ በደሴና ኮምቦልቻ ያወደማቸውንና ጉዳት ያደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች መልሶ ለማቋቋም ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቦታው ላይ ጊዜያዊ ቢሮ ከፍቶ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው፡፡

ጊዜያዊ ቢሮው ከክልሉ መሥተዳድር አካላት፣ ከባለድርሻዎች፣ ከባለሀብቶች፣ እንዲሁም ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ባደረገው ቅንጅታዊ ሥራ 11 የጨርቃጨርቅ፣ የምግብና መጠጥ እንዲሁም የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ምርት የማምረት ሥራ ጀምረዋል፡፡

የጊዜያዊ ቢሮው ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደገለጹት በአካባቢው የሚገኙ ባንኮች፣ ጉምሩክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ኤሌክትሪክ ኃይል ሥራ መጀመር ፋብሪካዎቹ ወደ ሥራ እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል። በቅርቡ ኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ሲለቀቅ ተጨማሪ ፋብሪካዎች ወደ ምርት እንደሚገቡ መገለጹን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleወደ ሀገር ለሚገቡ የዳያስፖራ አባላት የተዘጋጁ ኹነቶች ይፋ ኾኑ።
Next articleበአሸባሪው ትህነግ የወደመው የአለውሃ ድልድይ የግንባታ ሥራ ተጀመረ።