
ታኅሣሥ18/2014 ዓ.ም(አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ ሀገር ቤት በሚል ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የዳያስፖራ አባላት የተዘጋጁ የተለያዩ ኹነቶች ይፋ ኾኑ።
የሚመጡ እንግዶች አቀባበልና መስተንግዶ ለማስተባበር የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ የተደረገውን ዝግጅት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ወደ ሀገራቸው የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለመቀበል ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የተዘጋጁ ኹነቶችን ኮሚቴው ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ታኅሣሥ 20 የመክፈቻ መርኃ ግብር እንደሚካሄድ ኢዜአ ዘግቧል።
ታኅሣሥ 24 ደግሞ በአዲስ አበባ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ጉብኝት፣ ከታኅሣሥ 25 እስከ 27 በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ጉብኝት ማካሄድና ሌሎች መርኃግብሮችም ይፋ ተደርገዋል።
ዳያስፓራው ሀገርን መልሶ ለመገንባት ሊያደርገው በሚችለው አስተዋጽዖ፣ ኢንቨስትመንትና ሌሎች ሲፖዚየሞችም በመርኃ ግብሩ ተካተዋል።
የሚካሄዱት ኹነቶች የሚካሄዱበት ቀን እንደ አስፈላጊቱ ሊከለስ እንደሚችልም ተጠቁሟል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
