ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጥምቀትን በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀረበ፡፡

128

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጥምቀትን በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀረበ፡፡

ጎንደር፡ ታኅሣሥ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የተደረገውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዲያስፖራዎች እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የጥምቀት በዓልን በጎንደር እንዲያከብሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ እንዲሁም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በጎንደር ከተማ የጥምቀትን በዓልን ለማክበር ሁሉም ከውጭ የሚገቡም ሆኑ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲታደሙ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪ ማቅረቧን አስረድተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የተጓዱ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።


የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ በጥምቀት በዓል ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የተካተቱበት የባሕል ሳምንት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በጥምቀት በዓል የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ (ሹሩባ) በክብር ወደ ጎንደር የሚገባ መሆኑን ከንቲባው ገልጸው ይህንን ታሪካዊ ኹነት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጎንደር በመገኘት መታደም እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፡- ቃልኪዳን ኃይሌ

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Mudde 15/2014 ALI
Next articleወደ ሀገር ለሚገቡ የዳያስፖራ አባላት የተዘጋጁ ኹነቶች ይፋ ኾኑ።