የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተገናኘ የአመራር ለውጥ አደረገ።

389

ታኅሣሥ 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተገናኘ የአመራር ለውጥ አደርጓል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ በብሔረሰብ አስተዳደሩ በወረራ በቆየባቸው ወቅት ግድያ፣ ዘረፋ እና ንብረት የማውደም ተግባር ፈፅሟል። ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ እነዚህ ድርጊቶች በሽብር ቡድኑ ብቻ የተፈፀሙ እንዳልነበሩ ተመልክቷል።

በብሔረሰብ አስተዳደሩ የተወሰኑ የአመራር አካላት የአሸባሪዎቹን የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ሸኔ የጥፋት ተልእኮ ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ተገልጿል።

በተቃራኒው ሕዝቡን ከሁለቱ ቡድኖች ጥቃት ማኅበረሰቡን በመከላከል እስከ ሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራሮችም እንደነበሩ ምስክርነታቸውን የሰጡ ብዙ ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ በርካታ የዞኑ አመራሮችን ከኃላፊነት በማንሳት በአዲስ ተክቷል። ከሽብር ቡድኖቹ ጋር ያበሩ አካላትም በሕግ ቁጥጥር መዋላቸው ተገልጿል።

በምክር ቤቱ የተሾሙ አዲስ የልዩ ዞኑ አመራሮች ማኅበረሰቡን በማደራጀት የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ማስጠበቅ እና የዞኑ ነዋሪዎች በሽብርተኞቹ የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ሸኔ ካደረሱባቸው የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች እንዲያገግሙ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራቸው እንዲሆን ምክር ቤቱ አሳስቧል።

በብሔረሰብ አስተዳደሩ በሸባሪ ቡድኖች ምክንያት ከቤት ንብረታታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የመደገፍና ተቋርጠው የነበሩ የመንግሥት የአገልግሎት ተቋማትን ዳግም ሥራ የማስጀመር ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም የአስተዳደሩ አዳዲስ አመራሮች ለኢብኮ ተናግረዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

Previous articleአምባሳደር ካሳ ከበደ (ዶ.ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
Next article“መገን የራያ ልጅ መገን ጉራ ወርቄ የጀግኖቹ ቦታ ተመልከት እያለ ሠላሳ ተኮሶ ሠላሳ ሚመታ “