የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ሠራተኞች ማኅበር ጋር በመተባበር ለወልድያ ከተማ ነዋሪዎች 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ ድጋፍ አደረገ።

522

ወልድያ፡ ታኅሣሥ 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ሠራተኞች ማኅበር ጋር በመተባበር ለወልድያ ከተማ ነዋሪዎች 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ ድጋፍ አድርጓል።
አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን በወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ላይ በደል ፈፅሟል። ሀብትና ንብረታቸውን አውድሟል። ዜጎች ለረሃብ እንዲጋለጡ አድርጓል። የከተማዋ ነዋሪዎችም ከነፃነት በኋላ ደራሽ እና ዘላቂ ድጋፍ ይሻሉ።
የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ሠራተኞች ማኅበር ጋር በመተባበር ለወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ደራሽ የምግብ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሪት ቅድስት ግዛቸው ከአሁን በፊት ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ 44 ሚሊዬን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል። ለወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ቶሎ ለመድረስ ያለውን ነገር ይዘው መምጣታቸውንም ገልፀዋል። ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። የተደረገው ድጋፍ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑንም አንስተዋል
የአዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ሠራተኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት አምሳሉ አምባው ወልድያ የጀግኖች ሀገር መሆኗን እናውቃለን ብዙ መስዋእት ከፍላችኋልም ብለዋል። የተደረገው ድጋፍ በቂ ነው ብለው እንደማያስቡም ገልፀዋል። በወልድያ ከተማ ነዋሪዎች በደረሰው ችግርም ማዘናቸውን ተናግረዋል።

ጠላት ሕዝብና ሀገር ሊለያይ እና ሊበታትን ያሰበ ቢሆንም እኛ ግን የበለጠ እንድንገናኝ እና እንድንደጋገፍ እድል ፈጥሮልናል ነው ያሉት። ጠላት በ27 ዓመታት ያፈረሰውን እሴት በአጭር ጊዜ ውስጥ እየገነባው ነውም ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል ቤተሰብ የሚደርሰው በችግር ጊዜ መሆኑን ገልፀዋል። ችግር መልካም እድል ይዞ የሚመጣ መሆኑንም ተናግረዋል። ለተደረገው ድጋፍም አመስግነዋል። ለማኅበረሰቡ አሁንም ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ነው የተናገሩት። ሌሎች ዜጎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ-ከወልድያ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

Previous articleሀገር-አቀፉ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ እየተካሄደ ነው።
Next articleበሰላም ወቅት በጠመኔ፣ በጦርነት ወቅት በጦር መሳሪያ