ሀገር-አቀፉ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ እየተካሄደ ነው።

233

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር-አቀፉ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሚመሩት መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ታድመውበታል።
መድረኩ ከዚህ በፊት በባሕር ዳር ተካሂዶ በነበረው የመጀመሪያው መድረክ ሀገሪቱ ባጋጠማት የህልውና ዘመቻን አስመልክቶ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አጠቃላይ አፈፃፀም እና አሁናዊ ሁኔታን ይገመግማል።
በመድረኩ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይም ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። መረጃው የኢብኮ ነው
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

Previous article“የሀሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ያሳደረው ጫና እና መፍትሄው” የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
Next articleየአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ሠራተኞች ማኅበር ጋር በመተባበር ለወልድያ ከተማ ነዋሪዎች 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ ድጋፍ አደረገ።